16ሺህ የገጠር ቀበሌዎችን በኔትዎርክ በማገናኘት ከ17 ሚሊዮን በላይ አባላትን ያቀፉ የመጀመሪያ ደረጃ የህብረት ሥራ ማህበራትን በኔትዎርክ የግብይት ስርዓት በማስገባት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የገጠር ልማትን ማምጣት ይቻል ዘንድ ‹ዕልባት› በተባለ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የግል ካምፓኒ የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓም ተካሄደ፡፡
በአውደ ጥናት ላይ በተለያዩ ርዕሱች ማለትም ‹‹ICT development and Rural ICT Initiative in Ethiopia››, ‹‹ Developmental Role of Cooperative and Current Status››, ‹‹About Elebat Management and Technology Solution››, ‹‹Innovation and Concept of RIDSDON›› እና‹‹The Research Findings and Pilot Initiative›› በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ጥናቶች በተለያዮ አቅራቢዎች ቀርቧል፡፡ ከመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ህብረት ሥራ ኤጀንሲ፣ ከኢትዮቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በተገኙ ታዳሚወችም ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ዶ/ር አብዮት ባዩ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚ/ር የኤሌክትሮኒክስ መንግሥት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአውደ ጥናቱ እንዳስገነዘቡት የህብረት ሥራ ማህበራት የመረጃ ሃብታቸው በኔት ዎርክ ቴክኖሎጂ ተደግፎ ቀልጣፋ የግብርና ግብይት ሥርዓት ተፈጥሮላቸው የገጠሩን የፋይናንስ ሥርዓት በማዘመን የኤሌክትሮኒክ ቴክኖሎጂ ግብይት ውስጥ በማስገባት ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የገጠርና የአርሶ አደሩን ዕድገት ወደ ላቀ ድረጃ በአጭር ጊዜ ማሸጋገር የጋራ ዓላማ መሆኑ ጠቅሰው የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስፍላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡